`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 79/2016 መሰረት የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በመሆኑም ያሉትን ክፍተቶች በመሙላት ልማትና መልካም አስተዳደር በማረጋገጥ የተገልጋዩን ህዝብ እርካታ ለማረጋገጥ የለውጥ ስራ አመራር መሳሪያዎች የሆኑትን ቢፒአርና ቢኤሲሲ ቅንጅታዊ ትገባራን እውን በማድረግ ለውጡን ይበልጥ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ህዝብ የነቃ ተሳትፎ ኖሮት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ማደረግ አሰፈላጊ ነው፡፡

ስለሆነም ጽ/ቤቱ የሚሰጠው አገልግሎት ክፍለ ከተማውን የመስሪያ ቦታ የማልማት አቅምና የተገልጋይ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የመስሪያ ቦታ አቅርቦት በፍትሀዊነት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች ሊተገብሩትና ሊከተሉት የሚገባ ይህ የዜጎች ስምምነት ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ለአዲስና ነባር ኢንተርፕራይዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ከአድልዎ ነጻ በሆነ መልኩ በእኩልነትና በፍትሀዊነት ተደራሽ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ ነው።
  2. ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
  3. አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ፣
  4. በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች

    የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Mission and Vision ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ስለ አገልግሎቶች የተሟላ መረጃ የማግኘት፣ የመጠቀምና የሚጠይቀውን ወጭ የማወቅ ብት፣
  2. ተገቢውን አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር ማስተካከያ የመጠየቅ መብት፣
  3. ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት አላቸው፤
  4. በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ የማግኘት መብት፡፡ ፤
  5. ተገልጋዮች አገልግሎቱን ሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያላባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቸው፡፡፤
  6. የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት፣
  7. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያት/ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍታሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ የማግኘት መብት፣
  8. ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አግልገሎት የማግኘት መብት፤
  9. በጽ/ቤቱ ዕቅድ፣ ሪፖርትና ግብረ መልስ ላይ መሳተፍና አስተዋጽዖ የማድረግ፡፡ ፤
  10. ፍትሃዊና አድሎ የሌለበት አገልግሎት የማግኘት መብት፤

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. የአገልግሎት ሰጪ ተቋምን ሕጎችን የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
  2. ትክክለኛ መረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ
  3. የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላትና የማቅረብ ግዴታ
  4. የጽ/ቤታችን ህግና ሥርዓት የማክበር ግዴታ