image
image
image
image
image

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለ100 ኢንተርፕራይዞች እና ለ329 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ቁልፍ ርክክብ አካሄደ፡፡

ህዳር 27, 2018
ክፍለ ከተማው በዛሬው እለት የስራ እድል ለተፈጠረላቸው 100 የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን እና በውስጣቸው የሚገኙ 329 አንቀሳቃሾችን ቁልፍ አስረክቧል። የእድሉ ተጠቃሚ ለሆኑት ዜጎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ እንደተናገሩት መንግስት ለዜጎች ካለው የላቀ ክብር የስራ እድል በመፍጠር ብቁ ዜጋ እያፈራ ይገኛል ብለዋል። መንግስት ለዜጋው በተለይ ለስራ ፈላጊው ወገን ተቆርቁሮ የስራ እድል በመፍጠርና በማመቻቸት በሀገራችን ቀዳሚው የለውጥ አመራር ነው ያሉት ዶክተር ምስክር ከዚህም አኳያ ከሰባት አመት ወዲህ በየአመቱ በየክፍለ ከተማው፣ በየወረዳው፣ በየብሎኩ ያሉ የስራ እድል ያልተፈጠረላቸው ዜጎች በማኑፋክቸር፣ በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት፣ በከተማ ግብርና በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው እንዲሰሩ እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ በመለየትና በመመዝገብ በቴክኒክ እና በልዩ ልዩ ስልጠናዎች ከቴክኒክና ሙያና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት ስልጠና በመስጠት በማብቃት ወደስራ ከመግባታቸው በፊት ግንዛቤ እንዲይዙ ማድረግ ቀጥሎ ደግሞ መስሪያ ቦታ እና ሼዶችን እንዲሁም የተለያዩ ኢንተርፕራይዞችን በማመቻቸት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡ የተፈጠረላቹ የስራ እድል እናንተን፣ ቤተሰቦቻችንን ከመጥቀም አልፎ ለሀገር ጭምር የሚያበረክተው አሰተዋጽኦ ከፍተኛ ነው እናንተም ስራን ሳትንቁ ስራን አክብራቹ በተፈጠረላቹ የስራ እድል በመጠቀም የስራ እድል ላላገኙ ወገኖች ጭምር የስራ እድል ለመፍጠር በርትታቹ እንድትሰሩ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላፈዋል፡፡ በክፍለ ከተማው 199 ብሎኮች አሉ፤በእነዚህ ብሎኮች ላይ ምርታማነትን ከመጨመር፣ ስራ ከመፍጠር አኳያ ለበርካታ ዜጎች በስራ እድል ፈጠራ ላይ የሰራንበት ሁኔታ ነው ያለው ያሉት ደግሞ በክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመን ተስፋዬ ናቸው። መስሪያ መሸጫ ቦታ መስጠት ብቻ አይደለም የእኛ ሀላፊነት በቅርበት መከታተል፣ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ የክህሎት ክፍተት ካለም ሞልተን በተለይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚ ሁናችሁ በአካባቢያችሁ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ እንድትፈጥሩ ለማድረግ ከጎናችሁ ነን ሲሉም አቶ ዘመን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ